ክቡር አቶ ሙህዲን ሁሴን የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በመሆን በዞኑ የልማት፣ የሰላም፣ የመልካም አስተዳደር እና የህዝብ አገልግሎት ማሻሻያ ሥራዎችን በቅርብ በመመራት ላይ ይገኛሉ። የመንግስት ፖሊሲዎችን እና የልማት ፕሮግራሞችን በተቀናጀ መልኩ በማስፈፀም የዞኑን ዘላቂ ልማት፣ ሰላም እና የህዝብ ተሳትፎ ለማጠናከር በትጋት እየሰሩ ይገኛሉ።
አቶ ሀጂ ኑርዬ ኡንታሌ የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ እና የመንግስት ዋና ተጠሪ ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ። በፓርቲ አመራር፣ በመንግስት ሥራዎች ቅንጅት፣ በልማት ፕሮጀክቶች ክትትል እና በህዝብ አገልግሎት ማሻሻያ ዘርፎች ንቁ ሚና እያበረከቱ ይገኛሉ። የዞኑን ሰላም፣ ልማት እና መልካም አስተዳደር ለማጠናከር በትጋት እየሰሩ ይገኛሉ
ኢንጂነር አ/ቃደር አማን የሀላባ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የግብርና መምሪያ ኃላፊ በመሆን በዞኑ የግብርና ልማት፣ የምግብ ዋስትና፣ የአርሶ አደሮች ድጋፍ እና የገጠር ልማት ሥራዎችን በመምራት ከፍተኛ ሥራ እየሰሩ ይገኛሉ። እንዲሁም በዞኑ የመንግስት ሥራዎች ቅንጅት፣ ሰላም እና ልማትን ለማጠናከር በትጋት በመስራት ላይ ይገኛሉ።
አቶ አብዱልቃድር ኢ/ሎላሶ በሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ሆነው በፓርቲው የአደረጃጀት ሥራዎች፣ የአባላት ማጠናከሪያ፣ የመዋቅር ግንባታ እና የፓርቲ ፖሊሲዎች አፈጻጸም ላይ ከፍተኛ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛሉ። የፓርቲውን አደረጃጀታዊ ብቃት ለማሳደግ እና የአባላት ተሳትፎን ለማጠናከር በትጋት እየሰሩ ይገኛሉ።
አቶ ሀሩና አህመድ የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ፣ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ እንዲሁም የዞኑ የመንግስት ረዳት ተጠሪ በመሆን ያገለግላሉ።