የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት
EN
ተመለስ
የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት
ሐምሌ 13 2018 · 2 ወር በፊት news
በዞኑ የሚከናወኑ የበጎ ፍቃድ ተግባራት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት በላቀ ሁኔታ ልያረጋግጡ ይገባል፦ክቡር አቶ መሀመድከማል ኑሪዬ

በዞኑ የሚከናወኑ የበጎ ፍቃድ ተግባራት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት በላቀ ሁኔታ ልያረጋግጡ ይገባል፦ክቡር አቶ መሀመድከማል ኑሪዬ ሀምሌ፣13/2018"በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ"በሚል መሪ ቃል በዞኑ በተጠናከረ መልኩ እየተከናወነ የሚገኘውን የ2018 የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ ተግባራት እቅድ የእስካሁኑ አፈጻጸም ያለበት ደረጃ የዞኑ የበጎ ፍቃድ አብይ ኮሚቴ በዛሬው እለት ተገምግመዋል። ክቡር አቶ መሀመድከማል ኑሪዬ የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊና የዞኑ መንግስት ዋና ተጠሪና የዞኑ የበጎ ፍቃድ አብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ፓርቲያችን ብልጽግና የበጎ ተግባርን ባህል በማድረግ ዜጎችን ከችግር ለማላቀቅ አበክሮ እየሠራ የሚገኝ በመሆኑ ሁሉም የፓርቲው አመራር፣አባላት፣ ደጋፊዎች እንዲሁም መላው ህዝብ ለተግባራዊነቱ በአጽንኦት ልሠራ እንደሚገባ አሳስበዋል። በዞኑ የተቸገሩ ወገኖችን በተባበረ የድጋፍ ክንድ እራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ የተጀመረውን የበጎነት ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባም አስምረውበታል። በተለይም በየዘርፉ የሚገኘው አመራር ለክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት ባለቤት ሆኖ መንቀሳቀስ እንደሚገባው ተናግሯል። በዞኑ የሚከናወኑ የበጎ ፍቃድ ተግባራት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት በላቀ ሁኔታ ልያረጋግጡ ይገባልም ብለዋል። በተለይም አመራር የተፈጠረውን ምቹ አጋጣሚ አሟጦ በመጠቀም በ‎16ቱም የክረምት በጎ መስኮች ላይ ህብረተሰቡን በማሳተፍ በአጽንኦት መሥራት እንዳለባት አቶ መሀመድከማል አሳስበዋል። በዞኑ ‎በየአካባቢው የሚገኙ ሁሉም ወጣቶች የነጻ ጉልበት፣ገንዘብና ሀሳብ እንዲሳተፉ በማድረግ ሊስራ እንደሚገባ ሀላፊው ገልጸዋል። ‎ይህም የወጣቱን ሁለንተናዊ ስብዕና በመገንባት ወጣቱ ለለውጥ እንዲነሳሳ ብሎም ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን ይበልጥ እንዲያጎለብት ሚናው የጎላ ነውም ብለዋል። የሚከናወነው የበጎ ተግባር አፈጻጸሙ በየጊዜው እየተገመገመ መምራት እንደሚገባ የገለፁት ሀላፊውበአፈፃፀም ረገድ የተስተዋሉ ጉድለቶችን ፈጥኖ በማረም፣ጥንካሬዎችን በማጎልበት በትኩረት እንዲሠራም አስገንዝበዋል። ጥራቱ የጠበቀ የበጎ ተግባር በመሥራት፣ የአንድ እቅድ የአንድ ሪፖርት መርህን በመከተል ለህዝቡ ተጠቃሚነት አበክረን ልንሠራ እንደሚገባም አቶ መሀመድከማል አሳስበዋል። የሀላባ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ታገል ጌታቸው በዞኑ ዘንድሮ የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ ከ264, 653 በላይ ህ/ሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እና ከ3.7 ሚልዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብት ለማዳን ታቅዶ ወደተግባር መገባቱን ተናግረዋል። በችግኝ ተከለ፣በቤት ጥገናና እድሳት፣ በትምህርት፣በጤና፣ በግብርና፣ማእድ በማጋራት፣በአካባቢ ሰላም ማስጠበቅ እና በሌሎችም በጠቅላይ በ16ቱ ዘርፎች በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝም ሀላፊው ገልጸዋል።ሲል የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽህፈት ቤት ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ዘግቧል።

ፎቶዎች
አስተያየት
አስተያየቶች (0)

እስካሁን አስተያየት የለም። መጀመሪያ ይሁኑ!

ለመውደድ ወይም አስተያየት ለመስጠት ይግቡ።

ግባ ይመዝገቡ