የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት
EN
ተመለስ
የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት
ሐምሌ 13 2018 · 2 ወር በፊት news
‎የሀላባ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ የ2018 ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2019 ዕቅድ ዝግጅት ዙሪያ ግምገማ አካሄደ ።

‎የሀላባ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ የ2018 ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2019 ዕቅድ ዝግጅት ዙሪያ ግምገማ አካሄደ ። ‎የሀላባ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ የ2018 ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2019 ዕቅድ ዝግጅት ዙሪያ ግምገማ አካሄደዋል ። ‎ ‎ለመድረኩ የተዘጋጀውን የ2018 በጀት አመት አፈጻጸም ሪፖርት በዞኑ ሰላምና ፀጥታ ሀላፊ በአቶ ሙደስር ጎታጎ የቀረበው ስሆን በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ የሰላምና ጸጥታ ማስከበር ስራዎች፣ የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት የሚሹ አቅጣጫዎች ላይ ጥልቅ ውይይት ተደርጎባቸዋል ። ‎ ‎የሀላባ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ አቶ ሙደስር ጎታጎ ኃላፊው በበጀት ዓመቱ ከተከናወኑ ታላላቅና ታሪካዊ ስኬቶች መካከል 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በዞኑ ሙሉ በሙሉ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ስኬታማ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ የተደረገውን የተቀናጀ የጸጥታ ስራ በልዩነት አንስተው ምስጋናቸውን አቅርበዋል ። ‎ ‎አቶ ሙደስር በበጀት ዓመቱ ከተከናወኑ ታላላቅና ሌላኛው ታሪካዊ ስኬቶች መካከል አንዱ የሀላባ ሴራ በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲጠነቀቅ የዚህ ቤት አባለት ድርሻ ትልቅ ሚና የነበረቸው በመሆኑ በድጋሚ ምስጋናቸውን አቅርቧል ። ‎ ‎በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋሉ የጸጥታ ስጋቶችን ቀድሞ በመከላከል ረገድ አመርቂ ውጤት መመዝገቡ ያነሱት ስሆን የሰላም እሴቶችን ለማሳደግ ከአጎራባች ዞኖች ወረዳዎች ጋር ግጭቶችን በውይይት ለመፍታት ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከአማካሪ ምክር ቤትና ከወጣቶች ጋር በርካታ የምክክር መድረኮች መደረጉን ገልጿል ። ‎ ‎በዞኑ ሰላምና ልማትን የሚያደናቅፉ ግጭት ቀስቃሽ የሆኑ የሐሰተኛ መረጃዎች ስርጭትን ለመግታትና ሕጋዊ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝም አሳስበዋል ። ‎ ‎ሀላፊው አክለዉም የህዝቡን ዘላቂ ሰላምና ደህንነት ለማስፈን ጠንካራ የፀጥታ መዋቅርና የህዝብ አደረጃጃት ጥምረት መፍጠር እንደሚገባ ገልጸዋል። ‎ ‎የፀጥታ መዋቅሩ በየጊዜው ከሚከሰቱ ግጭቶችንና ወንጀሎችን አስቀድሞ የመከላከልና የመፍታት እንዲሁም ተቀናጅተው መሰራት እንዳለባቸው ነው ያሳሰቡት፡፡ ‎ ‎በዓላት የአብሮነት መገላጫ እየሆኑ በመምጣታቸው በጋራና በመተሳሰብ ማክበር እየተቻለ ከመሆኑም ባሻገር ህብረተሰቡ ሰላም ወዳድ መሆኑን ማየት የተቻለበት ነው ብለዋል። ‎ ‎ቀጣይም ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ቅንጅት በመፍጠር ህገ ወጥ ተግባራትን መካላከልና የፀረ ሰላም ሀይሎችን እኩይ ዓላማና ፍላጎት ማክሸፍ እንደሚገባ ተናግረዋል። ‎ ‎በመድረኩ የተገኙት የሀላባ ዞን ምክር ቤት ህግና ፍትህ አስተዳደር ዘርፍ ሀላፊ ክቡር ሁሴን ኢብራሂም በበኩላቸው ሰላም ለኢኮኖሚያዊ፣ ለማህበራዊና ለፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። ‎ ‎በዞኑ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የተጀመረውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንዲጠናከር ህብረተሰቡ በሰላምና በአከባቢ ፀጥታ ጉዳዮች የመምከር፣ የመነጋገር፣ ለሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮች የመፍትሄ አካል የመሆን ልምድ ማዳበር አለባቸው ብለዋል፡፡ ‎ ‎አፈፃፀምን መገምገም ጥንካሬና ድክመትን ለይቶ ለቀጣይ በጀት አመት ውጤታማ ስራዎችን ለመስራት የሚያግዝ መሆኑን ጠቅሰዋል። ‎ ‎በግምገማው መድረክ ላይ የሀላባ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት የመልካም አስተዳደርና ቅሬታ ሰም ጉዳዮች ዘርፍ ሀላፊ አቶ በሀሩ መሀመድ ፣ የሀላባ ዞን ሚሊሻ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ገመቹ ወርቅቾ፣ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ኑሪዬ፣ የአራቱም መዋቅር ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ሀላፊዎችና የፖሊስ አዛዦች፣ የዞኑ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ የማኔጅመንት አባላት እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካለት ተገኝተዋል። ‎ ‎ሲል የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽህፈት ቤት ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ዘግቧል ‎ወቅታዊ፣ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎችን ለመግኘት የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓ/ቅ/ጽ/ቤት የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ሊንክ ይጫኑና ይውደዱ!፣ይከታተላሉን!!.

ፎቶዎች
አስተያየት
አስተያየቶች (0)

እስካሁን አስተያየት የለም። መጀመሪያ ይሁኑ!

ለመውደድ ወይም አስተያየት ለመስጠት ይግቡ።

ግባ ይመዝገቡ