ተመለስ
የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት
በሀላባ ዞን የ2018 ትምህርት ዘመን 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት 98.88% ተማሪዎች 50% እና በላይ በማምጣት ወደ ቀጣዩ ክፍል ማለፋቸውን የዞኑ ትምህርት መመሪያ አስታወቀ
በሀላባ ዞን የ2018 ትምህርት ዘመን 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት 98.88% ተማሪዎች 50% እና በላይ በማምጣት ወደ ቀጣዩ ክፍል ማለፋቸውን የዞኑ ትምህርት መመሪያ አስታወቀ ሐምሌ 13/2018 የመምሪያው ኃላፊ ዶ/ር ኤፍሬም ዘለቀ እንደ ዞን 1,428 ወንድ 1,068 ሴት በድምሩ 2,496 ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ክልል-አቀፍ ፈተና የወሰዱ ሲሆን ከነዚህም 1,416 ወንድ 1,052 ሴት በድምሩ 2,468 (98.88%) ተማሪዎች 50% እና ከዚያ በላይ ውጤት በማስመዝገብ ወደ ቀጣዩ ክፍል ማለፋቸውን ተናግረዋል። በ2017 ዓ.ም ከነበረው 62.71% በ2018 ዓ.ም 98.88% ተማሪዎች ወደ ቀጣዩ ክፍል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ሲሆን 36.17% ከአምናው ጭማሪ ውጤት መመዝገቡንም ኃላፊው ገልጸዋል። የተመዘገበው ውጤት ባለፉት 5 ተከታታይ ዓመታት በዞኑ ትምህርት ሴክተር የተሰሩ ስራዎች ተጨባጭ ለውጥ ማምጣታቸውን ማሳያ ስለመሆኑ ዶ/ር ኤፍሬም አብራርተዋል። በመጨረሻም ይሄ የተመዘገበው ውጤት በቁልፍ ባለድርሻ አካላት ቅንጅት እና ጠንካራ ስራ የተገኘ በመሆኑ ነው ያሉት ኃላፊው ይህ ውጤት እንዲመጣ ሌት ተቀን ሳይተክቱ ለሰሩ ባለድርሻ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
አስተያየቶች (0)
እስካሁን አስተያየት የለም። መጀመሪያ ይሁኑ!