በዞኑ በ2018 በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግስት ስራዎች ከመቼዉም ጊዜ በላይ በቅንጅት በመሥራት አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ የተቻለበት ዓመት ነበር፦አቶ መሀመድከማል ኑሪዬ፣
በዞኑ በ2018 በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግስት ስራዎች ከመቼዉም ጊዜ በላይ በቅንጅት በመሥራት አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ የተቻለበት ዓመት ነበር፦አቶ መሀመድከማል ኑሪዬ፣ አቶ መሀመድከማል ኑሪዬ የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ በተገኙበት የዞኑ ፓርቲ ወቅታዊና መደበኛ ተግባራት የእስካሁን አፈጻጸም ያለበት ደረጃ በፓርቲው አመራር ኮሚቴ ተገምግሞ አቅጣጫ ተቀምጧል። በዚህም"ሁሉ አቀፍ እመርታ ለሁለንተናዊ ከፍታ"በሚል መሪ ቃል በቀጣይ ሁሉም ዘርፎች የሚከናወኑ የ2019 ዓ/ም የፓርቲ መደበኛ ተግባራት እቅድና፣እቅዱን ለማሳካት የተቀመጡ ግቦች አንጻር እንዲሁም በፓርቲው መሪነት እየተሠሩ ያሉ የክረምት የበጎ ሥራዎች አጠቃላይ የፓርቲው ሥራዎች አፈጻጸም እስከአሁን ያለበት ደረጃ ቀርቦ ተገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫዎች ተቀምጧል። በዚህ ወቅት አቶ መሀመድከማል ኑሪዬ በማዕከላዊ የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ በዞኑ በ2018 በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግስት ስራዎች በቅንጅት በመሥራት አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ የተቻለበት ዓመት መሆኑን ገልጸዋል። የተያያዝነው የተረጋጋና ሰላማዊ ዞን የመገንባት ግባችን ፊርያማ እየሆነ እንደሚገኝ ጠቁመው፣ዞኑን የተሞክሮ ማዕከልና የልምድ መቀመሪያ ዞን ለማድረግ የተያዘው ዕቅድ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱንም ሀላፊው ገልጸዋል። የምርጫና የልማት ስራዎች በአግባቡ በመመራታቸው የተያዙ ግቦች ማሳካት መቻሉንና የኢንሼቲቭ ስራዎች የህዝብ ተጠቃሚነትን እያረጋገጡ መምጣታቸውን፣ በሚዲያ አዎንታዊ የትርክት የበላይነት መረጋገጡ አቶ መሀመድከማል በስኬትነት ጠቅሷል። የሴቶችና የወጣቶች አደረጃጀቶች የተሻለ እንደነበር የገለፁት ሃላፊው፣በየዘርፉ የወጣቶችና ሴቶች ንቁ ተሳትፎ መኖሩን ተከትሎ የተሻለ ውጤት መምጣቱን፣የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት ጠንካራ ስራዎች መሰራታቸውንም ሀላፊ ጠቁመዋል። በአመቱ የአንድ ዕቅድ አንድ ሪፖርት አፈጻጸምና መናበብ የተሻለ እንደነበር ገልፀው በቀጣይም በጥራት መፈጸም እንደሚገባም ተናግሯል። ዓመቱ ጠንካራ የፓርቲ ተቋም መገንባት የተጀመረበት፣ ጠንካራ የአመራርና የአባላት የአቅም ግንባታ ተግባራት የተሰሩበት እና የህዝቡን ተጠቃሚነት ይበልጥ ማጎልበት የተቻለበት ዓመት እንደነበር የገለፁት ሀላፊው ለተመዘገቡት ስኬቶችም ሁሉንም ባለድርሻ አካላት አመሰግነዋለሁ። የ2019 ዓ/ም የፓርቲና መንግሥት ተግባራት እቅድ ከወትሮው በተለያ መልኩ አዳዲስ ስልቶችን በመቀየስና በመፈጸም በየዘርፉ እየተመዘገበ ያለውን ውጤታማነትን ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ሁሉም የፓርቲው አመራርና አባላት ግንባር ቀደም ሚና ሊወጡ እንደሚገባ አቶ መሀመድከማል አሳስበዋል። ሲል የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲቅ/ጽ/ቤት ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ዘግቧል፣ ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም፣ (ብልጽግና ኮሙኒኬሽን ወቅታዊ፣ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎችን ለመግኘት የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓ/ቅ/ጽ/ቤት የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ሊንክ ይጫኑና ይውደዱ!፣ይከታተላሉን!!.
እስካሁን አስተያየት የለም። መጀመሪያ ይሁኑ!