ተመለስ
የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት
የጉራጌ ልማት እና ባህል ማህበር በምስራቅ ጉራጌ ዞን"ጉዞ ወደ አረንጓዴ ልማት" 14ኛ ዙር የችግኝ ተከላ ፕሮግራም እየተካሄደ ነው
የጉራጌ ልማት እና ባህል ማህበር በምስራቅ ጉራጌ ዞን"ጉዞ ወደ አረንጓዴ ልማት" 14ኛ ዙር የችግኝ ተከላ ፕሮግራም እየተካሄደ ነው ሀምሌ፣25/2018)በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን በምስራቅ መስቃን ወረዳ "ጉዞ ወደ አረንጓዴ ልማት" 14ኛ ዙር የችግኝ ተከላ ፕሮግራም እየተካሄደ ነው የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር ላለፉት 13 ተከታታይ ዓመታት ባካሄደው የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ በገንባት ሂደት ጉልህ አበርክቶ እንደነበረውም ተመላክቷል። እንደ ሀገር "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሔደ የሚገኘውን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ታሳቢ በማድረግ ዘንድሮ ለ14ኛ ዙን የችግኝ ተከላ እየተካሔደ ነው። የጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር ባዘጋጀው የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ከፌደራል እና ከክልል የተውጣጡ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።ስል የዘገበው የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ነው።
ፎቶዎች
አስተያየቶች (0)
እስካሁን አስተያየት የለም። መጀመሪያ ይሁኑ!