"የታዳጊ ወጣቶች ለኢትዮጵያ ብልጽግና" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የወጣቶች የማስ ስፖርት በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር በድምቀት ተካሄደ!!!
"የታዳጊ ወጣቶች ለኢትዮጵያ ብልጽግና" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የወጣቶች የማስ ስፖርት በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር በድምቀት ተካሄደ!!! ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር "የታዳጊ ወጣቶች ለኢትዮጵያ ብልጽግና" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የወጣቶች የማስ ስፖርት እና የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በታላቅ ድምቀት ተካሂዷል። ይህ መርሃ ግብር በሀላባ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ እና በከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽሕፈት ቤት በጋራ አስተባባሪነት የተዘጋጀ ሲሆን የወጣቶችን አካላዊና አእምሯዊ ብቃት በማጎልበት ረገድ ትልቅ ሚና ያለው መሆኑ ተገልጿል። የሀላባ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ምክትልና የስፖርት ዘርፍ ሃላፊ አቶ አብደልባስጥ ናስር ስፖርት ከአካላዊ እንቅስቃሴና ጥንካሬ ባሻገር ለማህበራዊ እሴት ግንባታ፣ ለኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ለብሔራዊ መግባባት አይነተኛ መሣሪያ ነው ብለው ከዚህም በላይ የጋራ ዕሴት ነው ብለዋል። የስፖርት ልማቱን በመንግሥት ከተሰጠው ትኩረት ጎን ለጎን ዘላቂና ህዝባዊ መሠረት ያለው ለማድረግ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በትኩረት እየሰራን እንገኛለን። የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽሕፈት ቤት ሁላፊ አቶ ሳቢቱ በድሩ ስፖርትን ባህሉ ያደረገ ማህበረሰብ በመፍጠር ምርታማ ዜጋ ለማፍራት በትጋት እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ለዚህም ስኬት ከኢንተርናሽናል ስታዲየም ግንባታ ባሻገር በየደረጃው ያሉ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን በመገንባት ላይ እንገኛለን ብለዋል። የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ምትክልና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብደልፈታህ አብደላ በበኩላቸው ስፖርት የወጣቶችን ስብዕና ለመገንባት፣ ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብ ለመፍጠር እንዲሁም ለሰላም፣ ለአንድነትና ለብልጽግና ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል። በቀጣይም በጥቂት ቀናት ውስጥ በከተማችን የክረምት ልዩ ልዩ ስፖርታዊ ውድድሮች ስለሚካሄዱ ወጣቶች ተሳትፏቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ጠቁመዋል። በመጨረሻም በመርሃ ግብሩ ላይ የተሳተፉት ወጣቶችና የአካባቢው ነዋሪዎች የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ ከማድረጋቸውም በላይ የአረንጓዴ አሻራቸውን በማሳረፍ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አከናውነዋል።
እስካሁን አስተያየት የለም። መጀመሪያ ይሁኑ!