የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት
EN
ተመለስ
የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት
ሐምሌ 13 2018 · 2 ወር በፊት news
የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ አስተዳደር ዘርፍ ብልፅግና ህብረት የሚገኙ ብልጽግና ቤተሰቦች በልዕሳና ማዕከላዊ ጋዜጣ የጸና ሰላም፣የቀና ሥርዓት እንገንባ!በሚል አጀንዳ ዙርያ ዉይይት አደረጉ

የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ አስተዳደር ዘርፍ ብልፅግና ህብረት የሚገኙ ብልጽግና ቤተሰቦች በልዕሳና ማዕከላዊ ጋዜጣ የጸና ሰላም፣የቀና ሥርዓት እንገንባ!በሚል አጀንዳ ዙርያ ዉይይት አደረጉ የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የአስተዳደር ዘርፍ ብልፅግና ህብረት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብ/ፓ/ቅ/ፅ/ቤት በተዘጋጀዉ ልዕሳና ማዕከላዊ ጋዜጣ የጸና ሰላም፣የቀና ሥርዓት እንገንባ!በሚል አጀንዳ ዙርያ ዉይይትት አድርገዋል ። በዉይይቱ ላይ የተዘጋጀውን የጋዜጣ ፅሑፍ በአባላቱ በንባብ የቀረበ ሲሆን በጋዜጣው ዉስጥ በክልሉ የተመዘገቡ የልማት ስራዎች ፣ኢኮኖሚያዊ ፣ፖለቲካዊ እንዲሁም ማህበራዊ ጉዳዮችን መዳሰስ መቻላቸውን አንስተዋል ። በጋዜጣዋ ዉስጥ በሀገራችን በተካሄደው 7ኛዉ ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በሠላም መጠናቀቁን አስመልክቶ ምርጫው ከቀደሙት ጊዜያት በተለየ የህዝብ ተሳትፎ የጎላበተና ከልማት ስራዎች ጋር የተቆራኘ እንደነበረ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንደሻው ጣሰዉ(ዶ/ር) የገለጹበትም ነው። በቀጣይም የመረጠንን ህዝብ ለመገልገል ሁሉም አባላትና አመራር 24 ሰዓት መስራት እንደሚጠበቅባቸውና ለቀጣይ ብዙ መስራት እንዳለብን አቅጣጫ ጠቋሚ ጋዜጣ ነዉ ስሉ አባላቱ አስተያየታቸውን አክለዋል ። በመጨረሻም በምርጫው ወቅት የታየው ትብብር በክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት አገልግሎት መድገም እንደሚያስፈልግ ተወያዮቹ አፅንኦት ሰጥተዋል። ‎ሲል የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽህፈት ቤት ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ዘግቧል። ‎ወቅታዊ፣ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎችን ለመግኘት የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓ/ቅ/ጽ/ቤት የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ሊንክ ይጫኑና ይውደዱ!፣ይከታተላሉን!!.

ፎቶዎች
አስተያየት
አስተያየቶች (0)

እስካሁን አስተያየት የለም። መጀመሪያ ይሁኑ!

ለመውደድ ወይም አስተያየት ለመስጠት ይግቡ።

ግባ ይመዝገቡ