የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት
EN
ተመለስ
የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት
ሐምሌ 26 2018 · 1 ወር በፊት news
በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል ለሚካሄደው ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ ዝግጅት ተጠናክሮ ቀጥሏል!!

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል ለሚካሄደው ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ ዝግጅት ተጠናክሮ ቀጥሏል!!! በሐምሌ 27/2018 ዓ.ም "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚከናወነው ታላቅ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተሰራ ይገኛል። በከተማ አስተዳደሩ ችግኞቹን ለመትከል ሰፊ የቦታ ዝግጅት እየተደረገ የሚገኝ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮችም የችግኝ ተከላ ጉድጓድና የችግኝ አቅርቦት ስራው የደረሰበትን ደረጃ በቦታው ተገኝተው ምልከታ አድርገዋል። በዚህ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያላቸው ችግኞች በሚተከሉበት መርሃ ግብር ላይ የከተማችን ነዋሪዎች በሙሉ በነቃ ሁኔታ በመሳተፍ ሀገራችን የጀመረችውን የአረንጓዴ አሻራ ግብ ስኬታማ ለማድረግ የድርሻችሁን እንድትወጡ ጥሪ ቀርቧል። እንደ ከተማ አአስተዳደሩ በነገው ዕለት በአንድ ጀምበር ከከ68 ሺህ በላይ ችግኞችን ለመትከል በቂ ዝግጅት መደረጉን የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ግብርና ጽ/ቤት ገልጿል።

ፎቶዎች
አስተያየት
አስተያየቶች (0)

እስካሁን አስተያየት የለም። መጀመሪያ ይሁኑ!

ለመውደድ ወይም አስተያየት ለመስጠት ይግቡ።

ግባ ይመዝገቡ