የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት
EN
ተመለስ
የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት
ሐምሌ 13 2018 · 2 ወር በፊት news
በዞኑ በየደረጃው የተጀመሩ የ2018 ዓ.ም የክረምት ወረት የወጣቶች በጎ ፍቃድ አገልገሎት ተግባራት ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በዞኑ በየደረጃው የተጀመሩ የ2018 ዓ.ም የክረምት ወረት የወጣቶች በጎ ፍቃድ አገልገሎት ተግባራት ተጠናክሮ ቀጥሏል። በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ የ2018 ዓ.ም የክረምት ወረት የወጣቶች በጎ ፍቃድ አገልገሎት በወረዳው በሁሉም ቀበሌዎች በሁሉም ስምሪት መስኮች ወጣቱን በማስተባበር ከመቼውም በላይ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ይገኛል። ተግበዚህም መሰረት በወረዳው ታችኘው ሌንደ ቀበሌ በወረዳው ሰረተኛና ማህበራዊ ጉደይ ብልጽግና ቤተሰብ አማካይነት አበለቶችን በማስተባበር ለአንድ አቅመ ደካማ ቤተሰብ መኖርያ ቤት እየተገነባ ሲሆን ግንባታው በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቅቆ ለማስረከብ የሚያስችል የቆርቆሮና የምስመር፣የበርና መስኮት እንዲሁም የተለየዩ ቁሳቁስ በዛሬው ዕለት የወረዳው አስተባባሪዎች በተገኙበት ለቤተሰቡ ርክክብ አድርገዋል። በርክክቡ ላይ የተገኙት የዌራ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ የፖሎቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ጀማል አህመድ በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በመንግስት መሸፈን ያልተቻሉትን ተግባራት ወጣቱንና ማህበረሰቡን በማስተባበር እንዲሁም አቅም ለሌላቸው ምስክኖች ማረፍያ እንዲያገኙ አባላቶችን በማስተባበር ቤት እየተገነባለቸው መሆኑን በማሳሰብ ለዚህም በተቀናጀ ሁኔታ በየአካባቢያችን ያሉ አቅመ ደካሞችን ማገዝና መርዳት ከሁሉም የሚጠበቅ ተግባር መሆኑንም አሳስበዋል። ወጣቶች በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ ዘርፎች ተሳትፏቸዉ የላቀ እንዲሆን በየአካባቢው የሚገኙ ወጣቶች የክረምት ዕረፍት ጊዜያቸውን ህብረተሰብን በቅንነት በመገልገል ላይ መሰለፍ እንዳለባቸው የግንዛቤ ስራዎችንም በመጠናከር ቤቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቀው ማስረከብ እንዳለባቸው የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሙዘይን ጀማል ገልጸዋል። የአከባቢውን የወጣቶችና የሴቶች አደረጃጀቶችን በማስተባበር የጭቃ መለጠፍ ስራዎችንም በማቀላጠፍ በአጭር ጊዜ ውስጥ በጥረትና በፍጥነት በመጠናቀቅ ቤተሰቡን ከዝናብና ከፀሀይ ለመታደግ በትኩረት በመከታተል ጨርሰን የምናስረክብ ይሆናል ያሉት የወረዳው ሰረተኛና ማህበራዊ ጉደይ ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ በራቴ እሳ ነው። በመርሀግብሩ ላይም የዌራ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ምፍታ አወል፣የወረዳው ሰረተኛና ማህበራዊ ጉደይ ብልጽግና ቤተሳብ አባላቶች ፣የቀበሌው አመረሮች እንዲሁም አበለቶችና ሌሎችም ተገኝተዋል ። የወረደው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት

ፎቶዎች
አስተያየት
አስተያየቶች (0)

እስካሁን አስተያየት የለም። መጀመሪያ ይሁኑ!

ለመውደድ ወይም አስተያየት ለመስጠት ይግቡ።

ግባ ይመዝገቡ