የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት
EN
ተመለስ
የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት
ሐምሌ 13 2018 · 2 ወር በፊት news
በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ሰው ተኮር ተግባራትን ማዕከል ያደረገው የክረምት በጎ አገልግሎት ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ሰው ተኮር ተግባራትን ማዕከል ያደረገው የክረምት በጎ አገልግሎት ተጠናክሮ ቀጥሏል። ‎ ‎የብልጽግና ፓርቲ ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ የሆነውን ሰዉ ተኮር ተግባር "በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል የሚካሄደውን የክረምት የበጎ አድራጎት መርሃ-ግብር መሰረት በማድረግ፣ በዛላ ቀበሌ ለሚገኙ አቅመ-ደካሞች የአልባሳት ድጋፍ ተደርጓል። ‎ ‎በዚህ በጎ ተግባር ላይ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ ቤት ሀላፊ አቶ አ/መጅድ ፊጣሞ በቦታው ተገኝተው ድጋፉን ያስረከቡ ሲሆን፣ ወገንን መደገፍና አብሮነትን ማጠናከር የሁልጊዜም እሴታችን እንደሆነ ገልጸዋል። ‎ ‎"በጎነት የሰው ልጅ በጎ ሕሊና መግለጫና አብሮነታችንን የምናጠናክርበት ታላቅ እሴታች በመሆኑ በክረምት ወቅት ወገኖቻችንን በመደገፍና አብሮነታችንን በማሳየት የጀመርነውን በጎ ተግባር አጠናክረን እንቀጥላለን"ብሏል ‎ ‎በዚሁ የድጋፍ ማስረከብ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የሀላባ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ታገል ጌታቸዉ እንዳሉት፤ በጎ ፈቃደኝነት የርስ በእርስ ትስስራችንን የሚያጠናክርና የአቅመ ደካሞችን እፎይታ የሚያረጋግጥ ታላቅ ተግባር እንደሆነ ጠቅሷል። ‎ ‎አክለውም ወጣቶች በክረምቱ ወቅት በሚያካሂዷቸው በጎ ተግባራት አካባቢያቸውንና ሀገራቸውን በግንባር ቀደምትነት ሊደግፉ እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል ‎ ‎በመርሃ ግብሩ ላይ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ ቤት ሀላፊ አቶ አ/መጅድ ፊጣሞ፣የሀላባ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ታገል ጌታቸው፣የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ም/ሀላፊና የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሁሴን አብደላ እንድሁም የከተማና የቀበሌ አመራሮች ተገኝተዋል።

ፎቶዎች
አስተያየት
አስተያየቶች (0)

እስካሁን አስተያየት የለም። መጀመሪያ ይሁኑ!

ለመውደድ ወይም አስተያየት ለመስጠት ይግቡ።

ግባ ይመዝገቡ